ኢትዮጵያውያን በመጎስ ኣስገዶምና ኣብራሃም ዶቦጭ ምክንያት ኤርትራን ሳይከሱ ኣይቀሩም!

2121ተወልደበርሃን ገብረ

“ኣህያው ፈርታ ዱላውን” ይላሉ የኣማራ ሰዎች። ድስኩሩን በዩ-ትዩብ ለመስማት እዚጋ ተጫን። ጉዳዩ ስለ የካቲት 12 1929 የፋሽሽታዊው የጣልያን መንግስት ግፍ በኣዲስ ኣበባ ነው። ኣዎ እውነት ነው። ጣልይኖች ኣሰቃቂ እልቂት በኢትዮጵያውያን ላይ ፈጽመዋል። ከዛ በፊትም በኣይሮፕላን ጋዝ ተረጭቶባቸው ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ወገኖች በጣልያን ወራሪ ሀይል ኣልቀዋል። ነፍሳቸው ይማር። የኣዲስ ኣበባ ጭፍጨፋ ሊዩ የሚያደርገው ግን መነሻው በትውልድ ኤርትራውያን የሆኑ ሞጎስ ኣስገዶምና ኣብራሃም ዶቦጭ በጣሊያን ሽማምንቶች ባርከፈከፉት የቦምብ ጥቃት ለእልቂቱ መነሻ በመሆኑ ብቻ ነው። በኤርትራ ኣንድ ኣባባል ኣለ፡- “ጉይይ ካብ ምውዓል ክሳድ ምሓዝ”። በኣማርኛ ሲተረጎም “ቀኑን ሙሉ ከመሮጥ ዋናውን መንገድ መዝጋት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ሞጎስና ኣብራሃም ከዛ ውጭ ያሰቡ ኣይመስለኝም። ምኽንያቱም በወቅቱ ኢትዮጵያ በጣሊያን ቅኝ ግዛት ወድቃለች። ሞጎስና ኣብራሃም የፈጸሙት ጣሊያንን ለማዳከም መሪዎችዋን ማሸበርና መጨረስ የግድ ይሆናል ከሚል ሀሳብ የመነጨ ሊሆን እንደ ምችል ጤናማ ኣእምሮ ያለው ሰው የሚያስበው ይመስለኛል።

ኣሁን ኣሁን ግን ጥቂት ኢትዮጵያውያን በተገላብጦሽ ማሰብ ጀምረዋል። እሱም የሞጎስና የኣብራሃም ድርጊት ኢትዮጵያውያንን ለማስጨረስ ሆን ተብሎ የተቃጣ ድርጊት ሊሆን እንደ ምችል እየዛቱ ነው። ገና ያልተጠና ጉዳይ መሆኑም ይዝታሉ። እነ ፕሮፌሶር ሙሴ ተገኝ ከዛ ኣልፈው በመሄድ ኤርትራውያን ጠላቶቻችን ናቸው የነ ሞጎስና ኣብራሃም ድርጊትም ኤርትራውያን በኢትዮጵያውያን ያላቸው ጥላቻ መገለጫ ኣድርገው መግለጽ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። እነዚህ ማሰብ የተሳናቸው ኢትዮጵያውያን በወቅቱ ንጹሀኑ ኢትዮጵያውያን ለሞጎስና ለኣብራሃም ምን ስለ በደሉዋቸው ነው እልቂት የሚመኙላቸው? ለመሆኑ በወቅቱ ብዙዎች ኢትዮጵያውያን በየ ዱሩና ሸንተረሩ በጎበዝ ኣለቃ ኣማካኝነት ትግል ስያካይዱ ኣልነበሩንም? ከሆነሳ የሞጎስና የኣብራሃም ድርጊት ከዛ ትግል በምንድነው የሚለየው? እንዲይውም የሞጎስና የኣብራሃም ይሻላል ምኽንያቱም ጠላትን ድባቅ ለመምታት ቁንጮዎቹን በመምታት የፖለቲካ ምህዳሩን ስለሚያዳክም የበለጠ ዉጤት ይኖርሮዋል።

ፋሽሽቶች ግን ፈሪዎች ስለ ሆኑ ድርጊቱን በፈጸሙት ፋንታ በንጹሀኑ ላይ መበቀል መረጡ። ልክ ሀ/ስላሴና መንግስቱ ሀይለማሪያም በኤርትራውያን እና በራሳቸው ህዝብ የሆነውን የትግራይ ህዝብ እንዳ ኣደረጉት ማለት ነው። እውነትን መፍራት ለማንም ኣይበጅም። እና የፋሽስት ጣሊያን ድርጊት ከነዚህ ኣረመኔዎች መሪዎቻቸው በምንድነው የሚለየው? ሀ/ስላሴ ጦራቸው ስሸነፍ ንጹሀን ኤርትራውያን ቤቶቻቸው በእሳት እያጋዩ ታንኮቻቸው በኤርትራውያን ህጻናት፡ እናቶችና ኣዛውንት ላይ ላያቸው ኣልተራመዱም? ጀነራል ተሾመ እርገቱ (ገዳዩ ሰውየ) በታጋዮች ስለ ተገደሉ ብዙ መንደሮች እና ቀበሌዎች በመንግስቱ ጦር ለምሳሌ እንደ ዓዲ ኢብራሂም፡ ዖና፡ ገለብ፡ ኦምሓጀር፡ ወኪ-ዱባ፡ ሕርጊጎ፡ ሽዕብ እና ሌሎች ቀበሌዎች በእሳት ኣልጋዩም? በቤተ-ክርስትያን እና በመስጊድ ቤቶች ባጠለሉ ህጻናት፡ እናቶችና ኣዛውንቶች ኣሰቃቂ ግድያ ኣልተፈጸመም?

የፈለጋቹ ምክንያት ስጡት በትግራይ በሀውዜን ህዝብ በኣሰቃቂ መንገድ ህዝቡ በኣይሮፕላን ኣልተጨፈጨፈም? ጣልያን ያሁሉ ቢያደርግ ወንድምም እህትም ኣይደለም። ወገን ከምትለው ህዝብና መንግስት ኣሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸምብህ ግን በእጂጉ ይቆጫል። ለነገሩ እውነትን እንደ ደንብ በማይቆጠርበት መንደር ስለ እውነትን ማውራት እንቆቁሊሽ ነው። ኣሁን ኣሁን ጀግና የህዝብ ኣለኝታ ነበር እየተባለ በረዲዮ የሚሸለልለት የደርግና የሀ/ስላሴ ወታደር ያ በቀይ ሽብር ጊዜ ህዝብን ሲፈጅ የነበረ ጦር ኣይደለም? የሚገርመው የእነዚህ ጥቂት ሙሁር ተብየ ህሊና ቢስ ኢትዮጵያውያን እስከ መቸ ይሁን የኢትዮጵያ ህዝብ በጥላቻ የሚያወዛግቡት? ጥላቻ በመጫር የኢትዮጵያን ህዝብን ከወዲሁ ከኤርትራውያን ጋራ ለጦርነት ለማዘጋጀት ይሆን? ጥቂትም ቢሆኑ እነዚህ ሰዎች ኣላማቸው ዛሬም እንደ ወትሮ ለማያስቡለት ድሀ ኢትዮጵያዊ በስመ-ኣንድነት ወደ በህይወት የማይተርፍበት ጦርነት መማገድ ነው። እነሱ ኣይገቡም። ሌላ የድሀና የገበሬ ልጅ ግን እንደ ቅጠል እንዲረግፍ ይመኛሉ።

የሚገርመው ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግንነት ሲወሳ ሞጎስ ኣስጎዶም፡ ኣብራሃም ዶቦጭና ዘርኣይ ደረስን ስም ከፍ ማድረግ ስለ ጥላቻ ሲወራ ደግሞ ኤርትራውያንን በጥቁር ቀለም መቅባት ልምዳቸው ሆነ። እነዚህ ጀግኖች በፋሽሽቶች ጉያ ቦምብ ሲወረዉሩ ነፍስ ያላቸው ፍጡራን ናቸው። ግን ለህይወታቸው ከምንም ሳይቆጥሩ ድርጊቱን ፈጽመው በፋሽሽቶች እጅ ለወገኖቻቸው ሲሉ መስዋእት ሆነዋል። ህሊና ቢሶች ዘረኝነትን ስያወግዙ ሰምተናል። ታዲያ ከዚህ በላይ ዘረኝነት ኣለ እንዴ? ለነገሩ ስግብግቦች የሚሉትና የሚናገሩት ኣይገባቸዉም!!

ኣይገባቸውም እንጂ ለሞጎስና ለኣብራሃም ባሰቡት መንገድ ከፈረጁዋቸው ጣልያን ሳይሆን ኤርትራን ነው መክሰስ ያለባቸው። ምክንያቱም ሞጎስና ኣብራሃም ያ የጀግና ስራ ባይሰሩ ፋሽሽቶች ያን ዘግናኝ ድርጊት ኣይፈጽሙም ነበር። ኣሆ ባይሆን የኣዲስ ኣበባ የፋሽሽቶች ድርጊት ላይፈጸም ይችል ነበር። እንዲያ ከሆነማ ጣልያንን ሲወጋ የነበረ ኢያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊከሰስ ይገባል ማለት ነው። ምክንያቱም ከዛ በፊት በጣሊያኖች ስጨፈጨፍ የነበረ ሰላማዊ ህዝብ’ኮ ከኣርቦኞች ከፍተኛ ተቃዉሞ ይደርስበት ስለ ነበረ ነው። ስለዚ እነኛ ኣባት ኣርቦኞችም መከስስ ኣለባቸው ማለት ነው። እነዚህ ኣባት ኣርበኞች ጣሊያንን ባይወጉት ጣሊያኖችም ኣይበቀሉም ነበር ማለት ነው። ስግብግቦች ግን ምንም ቢሆን ምንም የሚሉትን ነገር ኣይገባቸውም።

መታወቅ የለበት ግን የነዚህ ጥቂት ህሊና ቢስ ኢትዮጵያውያን ዛቻቸው በሞጎስና በኣብራሃም ብቻ ሳይሆን ለኤርትራውያን ካላቸው ጥላቻ የሚነሳ መሆኑ መገንዘብ መታወቅ ኣለበት። የፈሪዎች ፉኮራና ዛቻ ከምንም እንደ ማንቆጥረው ግን መታወቅ ይገባል። ህዝቦቻችን ከማስታረቅ ፋንታ ጥላቻ የሚመርጡ ጥቂት ግለሰቦች በግዜ ካልተገቱ ኣፍራሽ ናቸውና ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያስቁማቸው ይገባል። እነዚህ ሰዎች የሚሉትና የሚናገሩት እርስ በርሱ የሚጫረስ ነው። ለዚህ ዘግናኝ የየካቲት 12 ድርጊት ተጠያቂዎች ሞጎስና ኣብራሃም ኮሆኑ ከዛ በፊት ለደረሰው ተመሳሳይ እልቂትም ኣባት ኣርቦኞች ተጠያቂ መሆን ኣለባቸው ማለት ነው። እይደለም?